ዩሴፍ መና ወራቆ ተወዳጁ የጌታ ባርያ ምድራዊ ሩጫቸውን ጨርሰው ጥቅምት 7፣2013 ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል።ለጌታ በነበራችው ጥልቅ ፍቀር ና መሰጠት ሌሎች እግዚአብሄር ራሱን ከፍጥረቱ ጋር ያስታረቀበትንሚስጢር የምስራቹን ቃል እንዲሰሙ ዘመናቸውን ኹሉ በልዩ ሸክም አግልግለዋል ፤ ሮጠዋል። መጋቢ ዩሴፍ በኢትዩጵያ ቤተክርስቲያን አሉ ከሚባሉ ስኬታማ ጸሀፍት ይመደባሉ።መጋቢ ዩሴፍ ከቦታ ቦታ በሚዘዋወሩባቸው ቦታዎች ኹሉ ንግግር በማቅረብም ይታወቃሉ።የወንጌል ማህበርተኛ በሚል ራዕይ በመነሳሳት ለወንጌላዊ ቀለብ ክርስቲያኑ ማህበረሰብ የተወሰነ ቋሚ ስጦታ በመመደብ ሚሸነሪዎችን ወንጌል ወዳልደረሰባቸው ቦታዎች መላክ እንደሚቻል ያሳዩ ባለ ራዕይ ናቸው። በመጋቢ ዩሴፍ ያላሰለሰ ጥረት ይህ በጎ ራዕይ በተለያዩ የወንጌላውያን ቤተ እምነቶች ውስጥ ተተግብረዋል ።ከእለታት ባንድ አሁድ ፣ መጋቢ ዩሴፍ ሶስት ጥንድ የወንጌል አገልጋዩችን ቤተክርስቲያን እንድትደግፍ እያነሳሱ ነበር።የዚያን ቀን አገልግሎት ካበቃ በኋላ ፣ሶስቱ ጥንድ ሚሸነሪዎች ለሚያስፈልጋቸው ነገር ሙሉውን የሚሸፍኑ ምእመናን መገኘታቸው አና በቀጣይም ለሚያስፈልጋቸው ነገር በገንዝብ እና በፀሎት ለመደገፍ ምእመናን ፈቃደኛነታቸውን አሳይተዋል።በአንድ ወቅት መጋቢ ዩሴፍን አንድ ሰው እንዲህ ሲል ገልጾአቸዋል ።በወንጌል ማህበርተኛ ዙርያ ድጋፍ ማድረግን በተመለከተ ሲናገሩ የሰማ ማንም ሰው ቢኾን የድርሻውን ከመወጣት አይቦዝንም።አክሎም መጋቢው ቤተ ክርስቲያንን ለወንጌል ማህበርተኛነት ሰለማደራጀት ሲናገሩ የመንፈሳቸውን ብርታትና ወኔውያቸውን ተራሮችን በሚሰነጥቅ ብርቱ ንፋስ መስሎታል መጋቢ ዩሴፍ ባጠቃላይ 15 መጻህፍት ጽፈዋል።የመጨረሻውቹ አራት መፃህፍት የተፃፉት በደም ካንሰር ህመም እየተጎሰሙ በነበረበት ወቅት ነው።ይህ ፕሮጀክት ሶስት አላማ ይዞ ይንቀሳቀሳል ፤ እነሱም አንደኛ በወንጌል ማህበርተኛነት ዙርያ መጋቢው ያዘጋጇቸውን መፃህፍቶች መተርጎም ፣መከለስ እና በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ብሎም ቤተ ክርስቲያንን ለአለም አቀፍ አገልግሎት በወንጌል ማህበርተኛነት ማደራጀት፤ኹለተኛ መፃህፍቶቹ በተደጋጋሚ እንዲታተሙና አንዲዳረሱ ፣ ሶስተኛ የመጋቢው የህይወት ታሪክ ተጽፎ ለንባብ እንዲውል፤ ወንድ ልጆቻቸው ታመነ ዩሴፍ ፣ተካልኝ ዩሴፍ እና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ይህንን ፕሮጀክት የመምራቱን ዋና ኃላፊነት የህይወት ታሪኩን በመፃፍ ከዚህ በፊት ለህትመት የበቁትን መፃህፍት በመከለስ እና መፃህፍቱን በማሰራጨት ይሳተፋሉ። ሲቀጥልም ይህ ፕሮጀክት በመጋቢው የተፃፉትን መፃህፍት በአገር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ማድረግ ነው።አላማው በዚህ ሳይወሰን ከመፃህፍቱ ህትመት የሚገኘውን ጥቂት ገቢ ለመጋቢ ዩሴፍ ውድ ባለቤት ለወይዘሮ ርብቃ ዲኖ እንደ ጡረታ አበል እንዲደርሳቸው ማድረግ ነው።
ለገቢ ማሰባሰቢያው ዘመቻ የፕሮጀክቱ ዋና የኮሚቴ አባላት ዶ/ር ኬት ኒኮላስ ፣አቶ ዘነበ ገብረ ሀና ፣አቶ ተካልኝ ዩሴፍ፣ዶ/ር ታመነ ዩሴፍ እና ዶ/ ር ቲም ጃኮብሰን ሲኾኑ ፤ በቀጣይነት የሌሎችን ሰዎች የስም ዝርዝር የምናካትት ይኾናል። ሲቀጥልም ይሄንን የገቢ ማሰባሰቢያ ለማስተዋወቅ ከሚረዱን ሰዎች ጋር እየሰራን እንገኛለን።ወገኖች ለቤተሰቡ እያሳዩት ያለው ድጋፍ እና ለመጋቢው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እየገለጹ ያሉበት መንገድ አበረታች እና ልብ የሚነካ ነው።እግዚአብሄር ልክ እንደ መጋቢው ስኬታማ እና ፍሬአማ አገልግሎት አገልግለን አንድናልፍ ይርዳን።በኢትዩጵያ ያሉ ወገኖች ይህን አካውንት በመጠቀም ፕሮጀክቱን ማገዝ ይችላሉ።የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ SWIFT Code: CBETETAA የአካውንት ባለቤቶች ዩሴፍ መና ወይም/እና ርብቃ ዲኖ። የአካውንት ቁጥር ፤1000269644943 አዲስ አበባ ኢትዩጵያ
ጌታ ይባርካችኹ